አዲስ ከሸማችነት ወደ አምራችነት

You are currently viewing አዲስ ከሸማችነት ወደ አምራችነት

AMN ታኅሣሥ 5/2018

በአዲስ አበባ ከተማ እተካሔደ ያለዉ ባለ ብዙ ዘርፍ የልማት አብዮት ስር-ነቀል ብቻ ሳይሆን አካታች እና ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰው ተኮር ነው የምንለው በምክንያት ነው ፡፡

ከተማችን አዲስ አበባ ልማቷ በህንፃ ጫካ ብቻ አለመወሠኗን በሌማት ቱሩፋት እና በከተማ ግብርና ከሸማችነት ወደ አምራችነት መሻገር መቻሏን ጭምር በተግባር አሳይታለች።

ለዚህ ማሳያ ከሆኑት ዉስጥ አንዱ የአቃቂ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል አይነተኛ መገለጫ ነው ፡፡

ልህቀት ማእከሉ በውስጡ የከብት ማድለቢያ ፣የወተት ላም እና እንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ፣:ዘመናዊ የመኖ ማምረቻ ሼዶችን እንዱሁም ምርት ማሳያና መሸጫ ሱቍች፣የመኖ ማስቀመጫ መጋዘኖች:የእንስሳት ክሊኒኮች እና :ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶችን በማካተት እና በማሳለጥ ለከተማዋ ህብረተሰብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ ይገኛል።

በሌላ በኩልም አርሶ አደሮች ሁለንተናዊ የእለት ከዕለት ስራቸዉን ከከተማ ኑሮ ጋራ በማስተሳሰር፣ ማምረት እንዲችሉ እና በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ኑሮን በዘላቂነት እንዲመሩ አስችሏል።

በተጨማሪም ገቢን በማሳድግ ብሎም የከተማዋ የምርት አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር በማድረግ ረገድም ጉልህ አስተዋፆኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ባለ ዘርፈ_ብዙ ማዕከል ነዉና በተፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ የከተማዋን እድገትና የዜጎችን ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሠል ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል። – የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review