አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አመታት እዉን ያደረገቻቸዉ መሰረተ ልማቶች መዲናዋ የቱሪዝም የስበት ማዕከል እንድትሆን እድልን ፈጥሯል

You are currently viewing አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አመታት እዉን ያደረገቻቸዉ መሰረተ ልማቶች መዲናዋ የቱሪዝም የስበት ማዕከል እንድትሆን እድልን ፈጥሯል

AMN – ታኅሣሥ 6/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮማሽን ያዘጋጀዉ 1ኛዉ የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ እየተደረገ ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አመታት እዉን ያደረገቻቸዉ መሰረተ ልማቶች መዲናዋ የቱሪዝም የስበት ማዕከል እንድትሆን እድልን ፈጥሯል ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች ምርጫ ትሆን ዘንድ ያሏትን ሀብቶች ማስተዋወቅ ይገባል ያሉት አቶ ሁንዴ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽንም በጉዳዩ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል፡፡

መሰል ፎረሞች የልምድ መቀመሪያ የቀጣይ የቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት መነሻ ናቸዉ ያሉት አቶ ሁንዴ በፎረሙ ላይ ፀጋዎችን ማሳየት ትብብርን ማላቅ እና መሰል ስራዎቸ ይሰራሉ ብለዋል፡፡

በፎረሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review