በስነ-ምግባር የታነፀ የአገልጋይነትን መንፈስ የተላበሰ የሰው ሀይል የማፍራት ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል

You are currently viewing በስነ-ምግባር የታነፀ የአገልጋይነትን መንፈስ የተላበሰ የሰው ሀይል የማፍራት ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል

AMN – ታኅሣሥ 6/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የአዳዲስ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና በኢትዮጲያ የሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ መስጠት ጀመረ ።

በስነ-ምግባር የታነፀ የአገልጋይነትን መንፈስ የተላበሰ የሰው ሀይል የማፍራት ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢንጅነር) ተናግረዋል ፡፡

መሬትና የሰው ሀብት የመዲናዋ ትልቅ ሀብት መሆኑን የገለፁት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ሀብት በፍታሃዊነት የሚያስተዳድር በእውቀትና በክህሎት የዳበረ የሰው ሀይል ወሳኝ መሆኑን አስተዋል ፡፡

በመዲናዋ ሪፎርም ከተደረገባቸው ተቋማት መካከል የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አንዱ መሆኑን የተናገሩት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በውስጡ ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማጥራት በርካታ የሪፎርም ስራዎች ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል ፡፡

አገልግሎቱን ከማዘመንና ዲጅታል ስርአትን ከመዘርጋትም ባሻገር በስነ-ምግባር የታነፅ የአገልጋይነትን መንፈስ የተላበሰ የሰው ሀይል ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከተማ አስተዳደሩም በዚህ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ሊዝ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁን ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተወጣጥተው በኤጀንሲው ስልጠና የጀመሩት አዳዲስ ተቀጣሪ ሰራተኞች የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ የሚታይባቸውና ለብልሹ አሰራር የተጋለጡ ቦታዎች ላይ ምደባ የሚሰጣቸው መሆኑንም ገልፀዋል ፡፡

በራሔል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review