የልጆች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የማተኮር አቅምን ይቀንሳል

You are currently viewing የልጆች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የማተኮር አቅምን ይቀንሳል

AMN – ታኀሣሥ 06/2018 ዓ.ም

የልጆች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የማተኮር አቅምን እንደሚቀንስ በፖርትላንድ የተካሄደ የጥናት ውጤት ይፋ ማድረጉን ዩፒ አይ አስነብቧል፡፡

ልጆች በፌስ ቡክ፣ በኢንስታግራም፣ በስናፕ ቻት፣ በቲክቶክ፣ በቲውተርና በሜሰንጄር ላይ ብዙ ጊዚያቸውን የሚያሳልፉ ከሆነ ቀስ በቀስ ትኩረት የመስጠት ችሎታቸው እየቀነሰ እንደሚሄድ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡

በስዊድን የካሮሊንስካ ኢንስቲትዩት የእውቀት (ኮግኒቲቭ ኒውሮሳይንስ) ፕሮፌሰር የሆኑት ቶርኬል ክሊንግበርግ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በልጆች ላይ ትኩረት የማድረግ ችሎታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ በጥናታችን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

የተደበላለቁ የማህበራዊ ድረ-ገጾችን የሚጠቀሙ ህፃናት የማተኮር ችሎታቸው እንደሚቀንስና ውጤቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተመራማሪዎች በጥናታቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

ተመራማረዎቹ አክለውም ግኝቱ ለወላጆች እና ለፖሊሲ አውጪዎች ጤናማ የዲጂታል አጠቃቀም የህጻናትን የእውቀት (ኮግኒቲቭ) እድገት የሚደግፉ ትክክለኛ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ እንደሚያግዛቸው በመረጃው ላይ ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review