ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና ያገኘው ፓርቲ የምክር ቤቱን የመጀመሪያ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩም ፓርቲው ያለፉትን ስድስት ወራት ያከናወናቸውን የስራ አፈጻጸም መገምገምን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባልና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊው አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ ተናግረዋል።
የ7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት ከአጀንዳዎች መካከል እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በዚህም ለምርጫው የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ለመምረጥ እና ቅስቀሳ ለማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።