የአዲስ አበባ ከተማ የቱሪዝም ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር ባለፉት የለዉጥ አመታት የተሰሩ ስራዎች በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ተጨባጭ ለውጥን አስመዝግቧል ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ አሁን ላይ ለኢትዮጵያዊያን ፍካት ለአፍሪካዊያን ኩራት ለአለምም የትኩረት ማዕከል እንደሆነች ገልፀዋል ፡፡
መዲናዋ ሁሉንም ቱሪስቶች ታሳቢ ያደረጉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እዉን ስለ ማድረጓ እና የዓለም ዓይኖች ሁሉ ማረፊያ እየሆነች መምጣቷን ነው አፈ ጉባኤዋ የተናገሩት፡፡
መሰል የቱሪዝም ፎረሞች የመንግስት እና የግሉን ዘርፍ ቅንጅት የሚያልቅ መዲናዋ ያሏትን የቱሪዝም እድሎችም በሚገባ ለማሳየት በር ከፋች ነዉ ብለዋል፡፡
በቀጣይም መዲናዋ የአለም የቱሪዝም መናገሻና መዳረሻ ትሆን ዘንድ መንግስት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
በተመስገን ይመር