በበጀት ዓመቱ 12 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያገኛሉ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ 12 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያገኛሉ

AMN ታኅሣሥ 6/ 2018 ዓ.ም

የግብርና ሚኒስቴር ከተረጂነት ወደ ምርታማነትና የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በግብርናው ዘርፍ መተግበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የግብርና አገልግሎቶች ከዲጂታል መታወቂያ ጋር እንዲተሳሰሩ መደረጉ በተለይ የግብርና ብድርን በማጎልበት የግብርና ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ተናግረዋል።

በቀጣይ የብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የፋይዳ መታወቂያው ሚና የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርዓያሥላሴ በበኩላቸው የፋይዳ መታወቂያ የተሟላ የግብርና መረጃ ዘዴ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን አንስተው፣ ምዝገባውም በቀጣይ ስድስት ወራት ውስጥ የሚከናወን እንደሆነ አስረድተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት 12 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንዲመዘገቡ ውጥን ተይዞ እየተሰራ ሲሆን የብድር ሥርዓቱን ከዲጂታል መታወቂያው ጋር በማስተሳሰር የግብርና ትራንስፎርሜሽንን እውን ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም 4.3 ሚሊዮን የሚሆኑ የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በዘላቂነት ለማሻገር በመድረኩ ስምምነት ላይ መደረሱን ግብርና ሚኒስቴት ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review