ለኢትዮጵያ ወርቅ ያስገኘችው ማህደር ደስታ ትልቅ ክለብ ለመግባት እየሰራች መሆኑን ተናገረች

You are currently viewing ለኢትዮጵያ ወርቅ ያስገኘችው ማህደር ደስታ ትልቅ ክለብ ለመግባት እየሰራች መሆኑን ተናገረች

AMN ታኅሣሥ 06 ቀን 2018 ዓ.ም

በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ለኢትዮጵያ ወርቅ ካስገኙ ስፖርተኞች አንዷ የሆነችው ብስክሌተኛ ማህደር ደስታ በቀጣይ ትልቅ ክለብ ለመግባት ጠንክራ እየሰራች እንደሆነ ተናግራለች።

ብስክሌተኛዋ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረገችው ቆይታ “በአስመዘገብኩት ውጤት ተደስቻለሁ ጠንካራ የቡድን ስራ መሰረታችን ለውጤት አብቅቶናል።” ስትል ተናግራለች።

የአየር ንብረቱ አስቸጋሪ እንደነበር የተናገረችው ማህደር ለብስክሌት ስፖርት ትኩረት ከተሰጠ በቀጣይም ውጤታማ ልጆችን ማፍራት እንደሚቻል ጠቁማለች።

በቀጣይ ፕሮፌሽናል ብስክሌተኛ የመሆን ህልሟን ለማሳካት ጠንክራ እንደምትሰራም ገልጻለች።

ከትግራይ ትራንስ ብስክሌት ክለብ የተገኘችው ማህደር ደስታ በአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ሁለት ወርቅ እና አንድ ብር በማምጣት ሀገሯ በብስክሌት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና እንድታጠናቅቅ ትልቁን ሚና ተወጥታለች።

በአለማየሁ ሙሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review