ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎችን በፖሊሲ እና በመንግስታዊ አሰራር ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ተሰርቷል

You are currently viewing ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎችን በፖሊሲ እና በመንግስታዊ አሰራር ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ተሰርቷል
  • Post category:ፖለቲካ

AMN- ታኅሣሥ 7/2018 ዓ.ም

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎችን በፖሊሲ እና በመንግስታዊ አሰራር ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ብልፅግና ፖርቲ የሚከተለው የተግባቦት ዴሞክራሲ ውጤት ነው” ሲሉ የብልፅግና ፖርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል።

”የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል ለሀገር ግንባታ ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ የብፅግና ፖርቲ ወጣቶች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፖርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ በፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ለሀሳብ የበላይነት ለንግግር ፖለቲካ እውቅና የሚሰጥ የዴሞክራሲ ባህል መገንባት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በካቢኔ ጉዳዮች እንዲሁ የፖሊሲ ረቂቅ ላይ መንግስት ተፎካካሪ ፖርቲዎችን ተሰታፊ ያደረገበት ሂደት ብልፅግና ፖርቲ የሚከተለው የተግባቦት ዴሞክራሲ ውጤት መሆኑን አክለዋል።

ወጣቶች እንደ ሀገር ለሚገጥሙ ችግሮች መፍትሄ እንጂ በሀገር ችግሮች ላይ ተጨማሪ ፈተና ሊሆኑ እንደማይገባም በንግግራቸው አንስተዋል።

በመድረኩ የዲሞክራሲ ባህል ምሰሶዎች በሚል የመወያያ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።

ወንድምአገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review