ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ለይፋዊ ጉብኝት በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት ሲሆን ውይይቶቻችን በጋራ የቅድሚያ ጉዳዮቻችን ላይ ትብብሮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል።