የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን በአፋር ክልል የጎና መካነ ጥናት ባደረገዉ ምርምር በአፋር ክልል ከ 1.5 ሚሊዮን በላይ ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረ የሰዉ ቅሪተ አካል ማግኘቱን አስታዉቋል፡፡
ቅሪተ አካሉ የተገኘዉ ስለሽ ሰማው (ዶ/ር) እና ማይክል ሮጀርስ (ዶ/ር) በተባሉ ተመራማሪዎች ነዉ፡፡

የፓሌዎ አንትሮፖሎጂ ተመራማሪዉ ስለሽ ሰማው በሰጡት መግለጫ በጎና መካነ ጥናት ግኝት እድሜው በአማካኝ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን አመታት የሚገመት የሰዉ ቅሪተ አካል ከተለያዩ የዘመኑ መገልገያ መሳሪያዎች ጋር መገኘቱን ይፋ አድርገዋል፡፡
አዲሱ የምርምር ግኝት የቅድመ ሰዉ ዝርያ አመጣጥ ታሪክ ላይ ያሉ መላምቶችን አዲስ ቅርጽ የሚያስይዝ መሆኑንም ተመራማሪዉ ገልጸዋል፡፡
እንደተመራማሪው ገለጻ የጎናው ግኝት ሆሞ ኢሬክተስ በአፍሪካ ውስጥ በአዝጋሚ ለውጥ ለአሁኑ ሰው ዝርያ መሠረት ወይም ግንድ መሆኑንና ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን የሚያጠናክር ግኝት ነው፡፡
በአልማዝ ሙሉጌታ