ኡስማን ዴምቤሌ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ

You are currently viewing ኡስማን ዴምቤሌ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ

AMN ታኅሣሥ 07 ቀን 2018 ዓ.ም

ኡስማን ዴምቤሌ የ2025 የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።

ፈረንሳዊው አጥቂ ዛሬ በኳታር ዶሃ በተደረገ ስነ ስርዓት ተፎካካሪዎቹን በልጦ የዓመቱ ምርጥ ተብሏል።

የ28 ዓመቱ ተጫዋች ከፓሪሰን ዠርማ ጋር ስኬታማ ዓመት አሳልፏል። በዚህ ስኬቱም የባሎን ዶ ኦር አሸናፊ እንደነበር አይዘነጋም።

በሴቶች የባርሰሎናዋ አማካይ አይታና ቦንማቲ ተመርጣለች።

የባርሰሎናዋ ተጫዋች ሽልማቱን ስታሸንፍ ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት ነው።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review