ጨቅላ ሕጻናት ከተወለዱ በኋላ መደረግ ያለበት ክትትል

You are currently viewing ጨቅላ ሕጻናት ከተወለዱ በኋላ መደረግ ያለበት ክትትል
  • Post category:ጤና

AMN- ታኅሣሥ 9/2018 ዓ.ም

ጨቅላ ሕጻናት ከተወለዱ በኋላ መደረግ ስላለበት ክትትል በተመለከተ ኤ ኤም ኤን የጨቅላ ሕጻናት ሀኪም ከሆኑት ዶክተር በሀይሉ በርታ ጋር ቆታ አድርጓል፡፡

ከተወለዱ እስከ ሃያ ስምንት ቀን ያሉ ህጻናት ጨቅላ ይባላሉ ያሉት ዶክተር በሀይሉ፣ በዚህ ወቀት የተለያዩ የጤና እክሎች እንደሚገጥማቸውም አንስተዋል፡፡

የጤና ችግር ሲገጥማቸው እንደየ ህመሙ ዓይነት ሆስፒታል ገብተው እንክብካቤ የሚደረግላቸው እና ህክምና የሚያስፈልጋቸው ከሆነ በሆስፒታል ተኝተው ካልሆነም ጊዜያዊ እርዳታ እና እክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡ ጨቅላ ሕጻናት ከተወለዱ እስከ ሃያ አራት ሰዓት ድረስ ገላቸውን እንዳይታጠቡ ይመከራል።

እምብርታቸው አከባቢ ሊደማ ስለሚችል ሁል ጊዜ መታየት አለበት ያሉት ባለሙያው፣ ዳይፐራቸው ሲታሰር እምብርታቸው እንዲደርቅ እና እንዲወድቅ መሸፈን እንደሌለበት እና ክፍት ሆኖ መታሰር እንደሚኖርበት ያስረዳሉ፡፡

ሀኪም የሚያዘው ቅባት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር እምብርታቸው ላይ መደረግ እንደሌለበት መክረዋል፡፡

ጨቅላ ሕጻናት ሲታመሙ የሚያሣዩት ምልክቶች

አንድ ሕጻን መታመሙን ከሚገልጽበት ምልክቶች መካከል ትኩሳት፣ መንቀጥቀጥ፣ ጡት መጥባት አለመቻል፣ የሰውነት ውስጥ የመድማት፣ ዝቅተኛ የሰውነት ሙቀት፣ የትንፋሽ መቆራረጥ ወይም ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፣ ሊገጥማቸው ስለሚችል፤ ሕጻናት የሚንከባከቡ ሰዎችና ወላጆች እነዚህን ምልክቶች እንዲከታተሉ አስገንዝበዋል።

የአመጋገባቸው ሁኔታን በተመለከተ

ጨቅላ ሕጻናቶች እንደ ተወለዱ የእናት ጡት መጀመር ይኖርባቸዋል።

በሁለት እና በሶስት ሰዓት ልዩነት እያፈራረቁ እስከ ስድስት ወር ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ወተት መጥባት እንደሚኖርባቸው እና ከስድስት ወር በኋላ ጡት ማጥባቱን በመቀጠል ተጨማሪ ምግቦች መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review