የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የሸቀጦችን አቅርቦት ለማስፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል

You are currently viewing የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የሸቀጦችን አቅርቦት ለማስፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል

‎AMN ታኅሣሥ 8/2018 ዓ.ም

‎የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የሸቀጦችን አቅርቦት ለማስፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምናጸጥታአስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

‎በቢሮው የሚመራው የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ፣ በህዳር ወር የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ገምግሟል።

‎በግምገማው ወቅት ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፣ መንግስት የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የሸቀጦችን አቅርቦት ለማስፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

‎ህብረተሰቡ በዋጋ ንረትና በአቅርቦት እጥረት የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች ለመፍታት፣ ከጎረቤት ከተሞች ጋር ያለውን የጋራ ስራ ማጠናከርና በኢኮኖሚ አሻጥር ላይ የተጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎‎የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልቢሮ ኃላፊና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በበኩላቸው፣ በህዳር ወር ያለ ንግድ ፈቃድ በሚሰሩ፣ ደረሰኝ በማይቆርጡ፣ ምርት በሚደብቁና የኢኮኖሚ አሻጥር በሚፈጥሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ የክትትልና የቁጥጥር እርምጃ ተወስዷል።

‎ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር የማስገባት ስራ ውጤታማ በሆነ መንገድ መከናወኑ ተገልጿል።

‎ህብረተሰቡ ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኝና የምርት አቅርቦቱ እንዲረጋጋ የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴው በቁርጠኝነት እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review