የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ ፣ ለሕዝቦቿ ነፃነት እና ለሁለቱ ሀገራት ከጥንት እስከ ዛሬ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ክብር ላሳዩት ልባዊ ፍቅር ታላቅ ምስጋና ይገባዎታል – ከንቲባ አዳነች ኤቤቤ

You are currently viewing የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ ፣ ለሕዝቦቿ ነፃነት እና ለሁለቱ ሀገራት ከጥንት እስከ ዛሬ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ክብር ላሳዩት ልባዊ ፍቅር ታላቅ ምስጋና ይገባዎታል – ከንቲባ አዳነች ኤቤቤ

AMN – ታኅሣሥ 8/2018 ዓ.ም

‎ከንቲባ አዳነች አቤቤ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ ፣ ለሕዝቦቿ ነፃነት እና ለሁለቱ ሀገራት ከጥንት እስከ ዛሬ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ክብር ላሳዩት ልባዊ ፍቅር ታላቅ ምስጋና ይገባዎታል ብለዋል፡፡

ከትላንት እስከ ዛሬ የዓለም መገናኛ ብዙኃን አበይት ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አዲስ አበባ /ኢትዮዽያ ቆይታ ላይ ያተኮረ ሆኗል ሲሉም ነው ከንቲባ አዳነቸ አቤቤ የገለፁት ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትራት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፤ በሁለቱ ጥንታዊ አገራት መካከል የነበረውን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጡን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ደማቅ ታሪክ በመጻፋችሁ የላቀ ክብር ይሰማናል ሲሉም በመልእከታቸው ገልፀዋል፡፡

አዲስ አበባ በአለም አቀፍ ደረጃ አዎንታዊ ተፅእኖ ፈጣሪነቷ ፣ የአሰባሳቢ ትርክት ሀሳብ አመንጪነቷ በአለም አደባባይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልፀዋ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review