የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግብርና ብድር አስጀመረ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግብርና ብድር አስጀመረ

AMN ታህሳስ 9/2018

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘላቂ ግብርናን ለመደገፍና የገጠር ኢኮኖሚ እድገትን ለማጎልበት ለአርሶና አርብቶ አደሮች የግብርና ብድርን በይፋ አስጀምሯል።

የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎቶች ምክትል ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ በወቅቱ የብድር አገልግሎቱ የአነስተኛ ባለ-ይዞታ አርሶና አርብቶ አደሮች የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

አገልግሎቱ አርሶ አደሮች በግልሰብ ደረጃም ሆነ ተደራጅተው ከግብርና ግብዓቶች እስከ ማሽነሪዎች ግዥ የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል።

ለእንስሳት ምርታማነት አርብቶ አደሮች የተለያዩ ግብዓቶች ለማሟላት ዕድል የፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል።

አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተመላክቷል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የግብርና ፋይናንስ በማሳደግ የገጠር ትራንስሮርሜሽንን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

መንግስት የግብርና ምርትና ምርታመነት ለማሳደግ የሚያስችሉትን በርካታ ተግባራት እያከናነ ይገኛል፡፡

ከዚህ ውስጥ አካታች የሆነ የፋይናንስ ተደረሽነትን በገጠር ማረጋገጥ መሆኑን ገልጸው፤ ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፋ ያደረገው የብድር አገልግሎት አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ባንኩ ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ የጀመረው አገልግሎት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑንም አመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review