ሸማች ህብረት ስራ ማህበራትን ለማዘመን የተከናወኑ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ።
ቋሚ ኮሚቴው የተለያዩ የህብረት ስራ ሸማች ማህበራትን ተዘዋውሮ ምልከታ አድርጓል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ጋቶች ወርድዮ በዚሁ እንዳሉት ሸማች ማህበራትን ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለማስቻል እየተከናወነ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ በሁሉም ሸማች ማህበራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል ለሚያከናውነው ተግባር ቋሚ ኮሚቴው ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽታዬ ሙሐመድ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ማህበራትን ለማዘመንና ዲጂታላይዝ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም አሰራርን ለማቀላጠፍና ለመቆጣጠር 2 ቴክኖሎጂዎችን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።

በደሳለኝ ሙሐመድ