የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለማህበረሰቡ መስጠት ያለባቸውን አገልግሎት እንዳይሰጡ በነዋሪዎች ታጥረው የተዘጉ መንገዶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
ከዋና መንገዶች ውጭ ያሉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ሁሉም ነዋሪ በእኩል እንዲጠቀሙባቸው የተሰሩ መሆናቸውን ያነሱት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ፣ በነዋሪዎች የተዘጉ መንገዶች ተከፍተው ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግም ግብረ ኃይል መቋቋሙን ገልጸዋል።

መንገዶቹን አጥረው የዘጉ ነዋሪዎችም በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ የማይከፍቱ ከሆነ፣ ባለስልጣኑ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የመንገድን ሀብት ከህገ-ወጥ ድርጊት ለመከላከል እና ለመጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተገልጿል።
በአይናለም አባይነህ