ከአዲስ አበባ ከተማ እድገት እኩል የሚጓዝ የፀጥታ ሀይል ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ተስፍዬ ደድር እንደገለጹት 22 ሺ 500 ለሚሆኑ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች እና የኮንዶሚኒዬም ማህበር ጥበቃዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
አዲስ አበባ በከፍተኛ የልማት ለውጥ ውስጥ መሆኗን ምክትል ቢሮ ሃላፊው አንስተው፣ ቢሮው ከእድገቷ እኩል የሚጓዝ የፀጥታ ሀይል ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
የጥበቃ ስራ ከራስም አልፎ ሌሎችንም ሰዎች፣ ተቋማትን እና አካባቢን የመጠበቅ ትልቅ ሀላፊነት ነው ያሉት ምክትል ቢሮ ኅላፊው፣ ሁሉም የጥበቃ ሰራተኞች፣ በዚህ ልክ ንቁና ቀልጣፍ ሆነውአካባቢያቸውን ሊቃኙ ይገባል ብለዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ሀይሌ በበኩላቸው መዲናዋን የሚመጥን አስተማማኝ ሰልምና ፀጥታ ለማስፈን ማህበረሰቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ ጀምሮ የሰላም ሰራዊቶችን በማስፍት እንደክፍለ ከተማ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አስተዋል።
ከፀጥታና ደህንነት ጋር ተያይዞ፣ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት መንገድ፣ እረቂቅ እና ዲጅታል መሳሪያዎችንም በመጠቀም እየሆነ መምጣቱ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን፣ የመንግስትን የጥበቃ አካላት ብቻ ሳይሆን፣ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎችምን የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ አካባቢያቸውን በንቃት መጠበቅ እንዲችሉ ግንዛቤ ለመፈጥር ያለመ ስልጠና ስለመሆኑም ተገልጿል።
በራሔል አበበ