በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከነዋሪዎች ጋር የእንጠያየቅ መድረክ መካሔድ ተጀምሯል።
በአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የተዘጋጀው የእንጠያየቅ መድረክ የሶስት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችንና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችን ፊት ለፊት ያገናኘ መድረክ ነው።
የንግድ ጽ/ቤት ፣የህብረት ስራ ጽ/ቤትና የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ነው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች እየተወያዩ ያሉት።
በመድረክ መልዕክት ያስተላለፉት የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ፣በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ሂደት ያልታዩ ችግሮችን ለመለየት የሚያስችል ነው ብለዋል።
ነዋሪው የሚያጋጥመውን ችግር ነቅሶ በማውጣት የተሻለ ስራ ለመስራት አቅም የሚፈጥር ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚው፣ ከመድረኩ የሚነሱ ጥያቄዎችንም የእቅድ አካል በማድረግ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

መድረኩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በመካሄድ ላይ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ ናቸው።
በመድረኮቹም አስፈጻሚ ተቋማትና የከተማዋ ነዋሪዎች ተቀራርበው እንዲሰሩ እድል የፈጠሩ ናቸው ብለዋል።
እለት ተእለት የሚሰጡ አገልግሎቶች የሚያጋጥሙ ችግሮች የሚታረሙበትን እድል የፈጠሩ መድረኮች መሆናቸውንም ነው ም/ቢሮ ኃላፊው የተናገሩት።
በፍቃዱ መለሰ