አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ጨምሮ 12 ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ጥምረት ፈጠሩ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ጨምሮ 12 ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ጥምረት ፈጠሩ

AMN – ታኅሣሥ 10/2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ጨምሮ 12 ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ጥምረት ፈጥረዋል፡፡

ይህ በፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብል ልማት ቢሮ የሚመራው ጥምረቱ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ክላስተር የሚሰኝ ነው።

ጥምረቱ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማ ለማድረግ፣ ወጥ አሰራርን በማዘጋጀት በመንግስት ተቋማት መካከል ትብብርን እና ቅንጅትን ለማጎልበት የሚያስችል የቅንጅታዊ አሰራር ስርዓት ሲሆን የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ መፍታት አላማ አድርጎ ይሰራል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ጨምሮ 12 ተቌማት በጋራ በሚሰሩበት “የአገልግሎት ና ቴክኖሎጂ ክላስተር” ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የህዝብ ድምፅነቱን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማስፍት፣ አገልግሎቱን በገለልተኝነት ለመፈተሽ እና ሎሎች ስራወችን ለማከናወን ሀላፊነትን በመረከብ ስምምነቱን ፈርሟል።

በቤተልሔም አየነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review