የፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን በሪፎርም የተከናወኑ ስራዎችን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኮሚሽኑ ያከናወነው የሪፎርም ስራ ስኬታማ መሆኑን ተናግረዋል።
ማህበራትን ለማዘመንና ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተሰራው ስራም ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል።
አዲስ አበባን የኢትዮጵያ ብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ የህብረት ስራ ማህበራት የድርሻቸውን መወጣት እንዲችሉ የሚያስችል ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሽታዬ ሙሐመድ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የህብረት ስራ ማህበራት መሆናቸውን አንስተዋል።
ኮሚሽኑ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ወደ ሪፎርም ከገባ ሁለት ዓመታትን ማስቆጠሩን ገልፀው ማህበራትን ለማዘመንና ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተሰራው ስራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በደሳለኝ መሀመድ