ብልጽግና ፓርቲ የአግላይ እና የበላይ እሳቤን በማፍረስ በእኩልነት እና በተግባቦት ዲሞክራሲ ግንባታ በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ያመጣ ፓርቲ ነው ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ የፓለቲካ እና አቅምግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ተናገሩ።
በአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅቤት የፓለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ለ3ኛ ጊዜ የሚካሄድዉ የአባላት የአሸናፊዎች አሸናፊ ጥያቄና መልስ ውድድር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ዉድድሩ ብቁ አመራር መፍጠር ጠንካራ ፓርቲን ለመገንባት ይረዳል በሚል መሪ ሃሳብ ከወረዳ ጀምሮ የፓርቲው እሳቤ ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥያቄዎችን በመመለስ ለአሸናፊዎች አሸናፊዎች ውድድር የበቁ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት መድረክ ነው።
በመርሀ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ የፓለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ሰማ ጥሩ ነህ (ዶ/ር) ፣ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ እና የፓለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራውን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ብልፅግና ፓርቲ የፓለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊሰማ ጥሩ ነህ (ዶ/ር ) በዚሁ ወቅት ብልፅግና ፓርቲ የአግላይ እና የበላይ እሳቤን በማፍረስ በእኩልነት እና በተግባቦት ዲሞክራሲ ግንባታ በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ያመጣ ፓርቲ ነው፤ በዚህም በስኬት እየተራመደ ይገኛል ብለዋል።
የፓርቲውን እሳቤ ወደ ማህበረሰቡ በማስረጽ አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት የማድረግ አላማ ያለውን መድረክ ላዘጋጁ የከተማው አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።
በመርሀግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ እና የፓለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው በበኩላቸው ፓርቲው በሀሳብ ልእልና የሚያምን አካታች ፓርቲ ነው፤ ለዚህም የሀሳብ ጥራት የውጤት መሰረት ነው ብሎ በማመን በሚያከናውናቸው ስራዎች ውጤት እያስመዘገበ ነው ብለዋል።
የጥያቄና መልስ ውድድሩ በ 11 ተወዳዳሪዎች መካከል እየተካሄደ ይገኛል።
በቤተልሔም አየነው