ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሰው ተኮርና ለሁሉም ሴክተሮች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሰው ተኮርና ለሁሉም ሴክተሮች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ነው

AMN- ታኅሳስ 11/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሰው ተኮርና ለሁሉም ሴክተሮች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ሲሆን በዲጂታል 2025 የተመዘገቡ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ስራውን በተጨባጭ ውጤት የምናሳይበት ጭምር ነው ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲጂታል አማካሪ ሚሪያም አሊ ገለጹ።

ስትራቴጂው በግልጽ የአስተዳደር ስርዓት፣ በሚለካ ውጤት እና በተጠያቂነት ላይ ተመስርቶ በቀጣይ አምስት ዓመታት ተግባራዊ ይሆናሉም ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ሁሉም የሚመለከተው አካል የጋራ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review