የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ሞሮኮ ከኮሞሮስ በሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ይጀመራል

You are currently viewing የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ሞሮኮ ከኮሞሮስ በሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ይጀመራል

AMN ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም

በሞሮኮ አዘጋጅነት የሚከናወነው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በይፋ ይጀመራል።

አዘጋጇ ሞሮኮ ከኮሞሮስ የሚያደርጉት ጨዋታ የውድድሩ መጀመርን ያበስራል።

ዋንጫ የማንሳት አቅም እንዳላት የተመሰከረላት ሞሮኮ በበርካታ ደጋፊዎቿ ታጅባ ትጫወታለች።

20ኛ የውድድሩ ተሳትፎዋን የምታደርገው ሞሮኮ አንድ ጊዜ የዋንጫው አሸናፊ ሆናለች።

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር እኤአ 1976 በኢትዮጵያ በተዘጋጀው ውድድር ላይ ያነሳችው ዋንጫ ብቸኛው የምትኮራበት ታሪኳ ነው።

በዋሊድ ሬግራጊ እየተመራች በ2022ቱ የኳታር የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ በመድረስ አህጉር ያኮራችው ሞሮኮ ሁለተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ለማንሳት ጥሩ አጋጣሚ ተፈጥሮላታል።

ኮሞሮስ በአንፃሩ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ ትሳተፋለች።

ሁለቱ ሀገራት ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሞሮኮ ሦስቱን አሸንፋ በአንዱ ነጥብ ተጋርታለች።

ምሽት 4 ሰዓት የሚጀምረው ጨዋታ ልዑል ሞሌይ አብደላህ ስታዲየም ላይ ይከናወናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review