ስኬት ፖርክ ሌላኛው የአዲስ አበባ መልክ

You are currently viewing ስኬት ፖርክ ሌላኛው የአዲስ አበባ መልክ

AMN ታኅሣሥ 14/2018

በመዲናዋ በተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለወጣቶች ምቹ እና ዘመናዊ የሆኑ በርካታ የስፖርት ማዘዉተሪያዎች ተሰርተዋል፡፡

ከነዚህ መካካል አንዱ የስኬት ፓርክ ነው፡፡

በከታማዋ ከአሁን ቀደም አንድ ስኬት ፓርክ ብቻ እንደነበረ እና በአሁኑ ጊዜ ግን ስድስት የስኬት ፓርኮች መሰራታቸዉን የሚናገሩት የስኬት ቦርድ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አወቀ ጀማነህ የስኬት ቦርድ ለመጓጓዣነት ከሚሰጠው አገልግሎት ባለፈ ለስራ ዕድል ፈጠራም እየዋለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኮሪደር ልማቱ ምቹ መንገዶች በመገንባታቸዉ ስኬተሮች ለትራንስፖርት እና ለመዝናኛ አገልግሎት እየዋሉ ነዉ፡፡

ስኬተር ብሩክታዊት ሳሙኤል ቀደም ባሉት ጊዜያት ስኬት ስንጀምር የከተማዋ ሁኔታ ምቹ ስላልነበር የተወሰነ መንገድ እስኬት እያደረግን፣ አብዛኛውን መንገድ በእጃችን ይዘን ነበር የምንሄደው ተላለች፡፡

አሁን ላይ የመዲናዋ መንገዶች ምቹ ሆነዉ በመገንባታቸዉ ተደራራቢ ጉዳይ ሲኖርብን ቶሎ ለመድረስ ስኬቶችን እንጠቀማለን ያለው ደግሞ ስኬተር እዮብ ቢኒያም ነው፡፡

ስኬተር ቃለአብ ዲታ በበኩሉ ከከተማዋ የኮሪደር ልማት በኋላ የስኬትም ሆነ የሳይክል መንገዶች ከመኪና መንገድ ውጭ ስለተሰራ በፊት ያጋጥመን የነበረውን አደጋ ሙሉ በሙሉ ቀንሶልናል ብሏል፡፡

አሁን ላይ ከዚህ ቀደም ያጋጥሙን የነበሩ ችግሮች ከከተማው መዘመን ጋር ተያይዞ ሙሉ በሙሉ ተቀርፈዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የመንገድ መጨናነቅ እና ምቹ ሁኔታ ካለመኖሩ የተነሳ ከመኪና ጋር እየተጋፋን ነበር እስኬት እና ሳይክል የምንነዳው፤ አሁን ግን በተሰራው ምቹ መንገድ ተጠቅመን በነጻነት ስኬት እደረግን ነው ያለው የሚለዉ ስኬተር ዳንኤል በቀለ ነው፡፡

በፍሬህይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review