ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መከሩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መከሩ

AMN – ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ከኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ገልፀዋል፡፡

የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

በጉብኝታቸው በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ገልፀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review