በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፉት “መደመር”፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት ሰው ተኮር በሆነ የብዝሃ ኢኮኖሚ ጉዞ ኢትዮጵያን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር አግዘዋል።
በእነዚህ መጻሕፍት የተነሱ እሳቤዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር የተገለጡና ለትውልዱ ብሩህ ተስፋን ያጎናጸፉ ናቸው። መጻሕፍቱ አሁን ከሕትመት ባሻገር በ Medemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው ቀርበዋል።
መተግበሪያው ይፋ በሆነበት መድረክም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመደመር እሳቤ የተከናወኑ ተግባራት ያስመዘገቡት ተጨባጭ ውጤት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቋሚ ዘጋቢዎች እንደበት መዳሰሳቸውን የጠቅላይ ሚኒትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡