የአካል ጉዳተኞችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአመለካከት ለዉጥ ማምጣት ያስፈልጋል

You are currently viewing የአካል ጉዳተኞችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአመለካከት ለዉጥ ማምጣት ያስፈልጋል

AMN – ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የአካል ጉዳተኞች ቀን በአዲስ አበባ ደረጃ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በመካሔድ ላይ ይገኛል።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ፤ ቀኑ ስለ አካል ጉዳተኝነት ግንዛቤ የሚፈጠርበት ብቻ ሳይሆን የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚጠቅም ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የአካል ጉዳተኞችን ቀን ማክበር የአካል ጉዳተኞችን መብት በማስከበር ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝና የአካል ጉዳተኞችን ክህሎት በማዳበር፣ ፓሊሲም ጭምር ለመቅረፅ የሚያስችል ነው ሲሉ የቢሮው ኃላፊ ገልፀዋል።

እንደ ከተማ አስተዳደር አካል ጉዳተኞች በተለያዮ ዘርፎች ተደራጅተው እንዲሰሩ ከማድረግ ባለፈ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆነች ከተማ እየገነባ ይገኛል ብለዋል።

የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

የአካል ጉዳተኞች ቀን “አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።

የአካል ጉዳተኞች ቀን የማጠቃለያ ፕሮግራም በከተማ አቀፍ ደረጃ በአድዋ ሙዚየም በተለያዩ መሰናዶዎች እየተካሄደ ይገኛል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review