የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከቻይና የሕዝብ ደህንነት ሚኒስቴር ለVIP ጥበቃና እጀባ እንዲሁም ለፈጣን መንገድ (Highway) ትራፊክ ቁጥጥር የሚያገለግሉ ዘመናዊ ሞተር ሳይክሎችን ከሞተረኞቹ አልባሳት ጋር በድጋፍ አግኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሪፎርም ወዲህ በብዙ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ እየዘመነ የመጣ ተቋም ሲሆን በቅርቡ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን፣ ለሰርቪላንስና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ድሮኖችን የታጠቀ እና አሁን ላይ ደግሞ ለእጀባና ለፈጣን መንገድ (Highway) ትራፊክ ቁጥጥር የሚያገለግሉ ዘመናዊ የሞተር ሳይክሎችን ተረክቧል።

ሀገራችን የተለያዩ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶችን የማስተናገድ አቅሟ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ በሁነቶቹ ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀገራችን የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ የሀገርን ገጽታ በሚመጥን ክብር ለማጀብ እንዲሁም የከተማችንን የትራፊክ ፍሰት ለማሳለጥ ዘመናዊ ሞተር ሳይክሎቹ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ አስታውቋል ።