የኢትዮጵያውን አማዞን ለመፍጠር የተነሳው ወጣት ስራ ፈጣሪ

You are currently viewing የኢትዮጵያውን አማዞን ለመፍጠር የተነሳው ወጣት ስራ ፈጣሪ

AMN – ታኀሣሥ 15/2ዐ18 ዓ/ም

የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሰውን ልጅ ህይወት እያቀለሉ ባለበት በዚህ ዘመን፣ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በፈጠራ ስራዎቻቸው ዓለምን እያስደመሙ ይገኛሉ። ከእነዚህ አንዱ የቲና ማርት (TINA MART) መስራችና ስራ አስኪያጅ ወጣት ኢዘዲን ካሚል ነው።

ኢዘዲን ገና ዩኒቨርሲቲ ሳይቀላቀል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ሰላሳ ሰባት የፈጠራ ስራዎችን የሰራ ድንቅ ወጣት ነው። ከስራዎቹ መካከል በፀሐይ ኃይልና በኤሌክትሪክ የሚሰራ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪና ስብሰባ አዳራሽ ሲገባ ስልክን በራሱ “ሳይለንት” የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ይገኙበታል።

ከእነዚህ የፈጠራ ስራዎቹ መካከል 13ቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያስገኙለት ሲሆን፣ በዚሁ ስራውም የተለያዩ የዓለም ሀገራትን የመጎብኘት እድል አግኝቷል።

ኢዘዲን አሁን ላይ ትኩረቱን ወደ ቢዝነስ በማዞር “ቲና ማርት” የተሰኘ የኢ-ኮሚርስ መተግበሪያን አበልፅጓል። በዚህም ለሃያ ስደስት ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

300 የሚጠጉ ሻጮችን ማለትም የጃፋር መጻሕፍት መደብር፣ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ የንግድ ተቋማት በቲና ማርት በኩል ምርቶቻቸውን ለመሸጥ አስመዝግበዋል፡፡

ተቋማቱ ከ4 ሺህ በላይ ምርቶችን ለገበያ ማቅረባቸውን ወጣቱ ሥራ ፈጣሪ ይናገራል፡፡ 17 ሺ የተመዘገቡ ገዢዎች ያለው ሲሆን፣ በየትኛውም ቦታና የዓለም ክፍል ለሚገኙ ደንበኞች አገልግሎት ይሰጣል።

“ሀገራችን ወደ ዲጂታላይዜሽን እየተሸጋገረች ነው” የሚለው ኢዘዲን፣ መንግስት ያጸደቀው የስታርት አፕ (START-UP) አዋጃ እና የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና ለዘርፉ ትልቅ መነቃቃት እንደሚፈጥር ያምናል።

የኩባንያው ዓላማ የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት በማዘመን “የኢትዮጵያ አማዞን ገበያ” ን መፍጠር ነው።

በቲና ማርት የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶችም በተፈጠረላቸው ዕድል ካገኙት ጥቅም በተጨማሪ፤ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዕውቀት እየቀሰሙ መሆናቸውንና ወደፊት የራሳቸውን ስራ ለመፍጠር ትልቅ መነሻ እንደሆናቸው ተናግረዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review