AMN -ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጪውን የፈረንጆች ገና በዓል ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ ኮር አባላት እና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መግለጫ፣ የገና በዓል የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
ከንቲባዋ ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት የሚከተለው ነው።
“የበዓል ሰሞን እየተቃረበ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በአዲስ አበባ ለምትገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ልባዊ የሆነ የገና በዓል ምኞቴን አስተላልፋለሁ። አዲሱ ዓመታችሁም የሰላም፣ የደስታ እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። መልካም የገና እና የአዲስ ዓመት በዓል ይሁንላችሁ!”