የፌደራል እና የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት የገበያ ትስስር መድረክ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የፌደራል እና የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት የገበያ ትስስር መድረክ እየተካሄደ ነው
  • Post category:ቢዝነስ

AMN – ታኀሣሥ 16/2018 ዓ/ም

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ አመራሮችና ዩኒየኖች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

አቶ አወሉ አብዲ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ባለፉት አመታት ለግብርናው ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት ምርት እና ምርታማነት መጨመሩን ተናግረዉ የኑሮ ዉድነትን ማረጋጋት የሚያስችል ምርት በጥራትም በብዛትም መኖሩን አረጋግጠዋል::

የተርጋጋ የግብይት ስርዓት እንዲኖር በባለቤትነት መስራት እንደሚገባ የተናገሩት አቶ አወሉ በገቢያ ዉስጥ ያሉ ደላሎችን ሕግ ማስያዝ ይገባል ብለዋል ::

ዩኒየኖች ያልተቋረጠ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ስራቸዉን አጠናክረዉ መቀጠል እንድሚገባቸው የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ናቸው። ከተማ አስተዳደሩ ገቢያው የተረጋጋ እንዲሆንም በርካታ ስራዎች መሰረታቸዉን ገልፀዋል ::

በዚህ ረገድም የክልል እና የአዲስ አበባ ዩኒየኖች በመቀናጀት በርካታ ስራዎች ሰርተዋል ያሉት ምክትል ከንቲባው ዩኒየኖችን የመደገፍ እና የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ::

የፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሸነር አቶ ጌትነት ታደሰ ህብረት ስራ ማህበራት ተወዳደሪ እና አካታች እንዲሆኑ የተለያዩ ተግባራት ተከናወነዋል ብለዋል::

ዘላቂነት ያለው ትስስር በመፍጠር ገቢያዉን የማረጋጋት ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል ::

የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ አምራች እና ሽማቹ ገቢያ በማስተሳሰር በተሰራዉ ስራ የሸቀጦች ዋጋ እንዲረጋጋ እና የአቅርቦት ችግር እንዲቃለል አስችሏል ብለዋል::

ቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review