የእንጠያየቅ መድረክ ነዋሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄ በቀጥታ ምላሽ እንዲያገኙ አስችሏል

You are currently viewing የእንጠያየቅ መድረክ ነዋሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄ በቀጥታ ምላሽ እንዲያገኙ አስችሏል

AMN- ታኀሣሥ 16/2018 ዓ.ም

ነዋሪው ጥያቄውን በቀጥታ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ምላሽ እንዲያገኝ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት ከሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ፣ደንብ ማስከበር፣ፍትህ እና አካባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ጋር የእንጠያየቅ መድረክ ተካሂዷል ።

በመድረኩ የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ለመመለስና በየተቋሙ ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የህዝብ እንጠያየቅ መድረክ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ፈይሳ ከለውጡ ማግስት በክፍለ ከተማው በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት እየተከናዎኑ መሆኑን ጠቅሰው የእንጠያየቅ መድረክ በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ሂደት ያልታዩ ችግሮችን ለመለየት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚኪያስ አውቀነው መድረኩ ከነዋሪው በኩል የሚነሱ ጥያቄዎች በቀጥታ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል ዘንድ በማገናኘት የነዋሪውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ ከደንብ ማስከበር፣ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር፣ አካባቢ ጥበቃ እና ፍትህ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በስፋት የተነሱ ሲሆን ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የእንጠያየቅ መድረኩ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

በሃብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review