” ብሔራዊ ጥቅምና ሚዲያ በሚል መሪ ሀሳብ ” 48ኛው የ”ጉሚ በለል” የውይይት መድረክ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ውይይት እየተካሄደ ።
የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐይሉ አዱኛ ሚዲያ ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አበርክቶ አለው ብለዋል።

በሚዲያ ስራ የሚዲያ ነጻነት እንደተጠበቀ ሆኖ በዜጎች መካከል ጥርጣሬ የሚፈጥር እና መራራቅን የሚሰብክ ሀሳብን ማራቅ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
ሚዲያ ብልሹ አሰራሮችን በማጋለጥ ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል ።

በሚዲያው ዘርፍ የተሰማራ ማንኛውም ዜጋ የአፍሪካ ቀንድ ጂኦፖለቲካ በመረዳት የሀገር ብሄራዊ ጥቅም በማስከበር መልኩ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሚዲያን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ሀገርን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያቻልም ተናግረዋል ።
በ48ኛው ዙር ጉሚ በለል መድረክ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ጨምሮ የሚዲያ ኃላፊዎች ፣ ባለሙያዎች እና ምሁራን እየተሳተፉ ነው ።
በዳንኤል መላኩ