ብሔራዊ ጥቅም በቡድን ፣ በጊዜ ፣ በተቋም አይገደብም ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ገለፁ
ብሔራዊ ጥቅምና ሚዲያ በሚል መሪ ሀሳብ 48ኛው የ ጉሚ በለል የውይይት መድረክ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህ ወቅት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፣ የአንድ ሀገር ብሄራዊ ጥቅም በቡድን ፣ በጊዜ ፣ በተቋም አይገደብም ሁሌም በትውልድ ቅብብሎሽ ተመሳሳይ አቋም የሚያዝበት ነው ብለዋል ።

ውስጣዊ አንድነት ከማጠናከር እና ብሄራዊ ጥቅም ከማስከበር አንጻር የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን እና ሀሰተኛ መረጃዎች ከመዋጋት አንጻርም ሚዲያዎች ኃላፊነታቸው መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል ።

የሀገር ደህንነት እና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሂደትም ሚዲያ የማይተካ ሚና እንዳለውየገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ተደማጭነት ለማረጋገጥ የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።
በዳንኤል መላኩ