ካፍ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ላይ ቅጣት መጣሉን አሳውቋል፡፡
ሀገሪቱ ቅጣት የተጣለባት በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ዚምባብዌን ከረታች በኋላ ለብዙሃን መገናኛ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኗ ነው ተብሏል፡፡
የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ከከባድ ማስጠንቀቂያ ጋር የ5ሺ ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንድትከፍል ተበይኖባታል፡፡
ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ደቡብ አፍሪካን የምትገጥመው ግብፅ ከጨዋታው በኋላ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ካልሆነች ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃት ካፍ አስጠንቅቋል፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ