የአሜሪካዋ ግዛት ኒውዮርክ በበረዶ መሸፈን የጉዞ መስተጓጎልም አስከትሏል፡፡
ከዓለም ዋና የንግድ፣ የፋይናንስ እና የባህል ማዕከላት መካከል አንዷ የሆነችው ኒውዮርክ ከተማ፣ ማለዳ የነቃችው በከፍተኛ በረዶ ተሸፍና ነው፡፡
ይህ ክስትት የክረምት አውሎ ነፋስ የሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ክፍልን ከከደነ በኋላ በኒውዮርክ ሲያጋጥም አራት ዓመታት ገደማ ሆኖታል፡፡
የኒዎዮርክ ብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እንደገለጸው፣ የከተማ ማዕከላዊ ፓርክ ከፈረንጆቹ ጥር 2022 ጀምሮ ከፍተኛ የተባለውን 11 ሴንቲ ሜትር ከፍታ በደረሰ በረዶ ተሸፍኗል፡፡
ሌሎች የግዛቲቱ ክፍሎች ደግሞ እስከ 19 ሴንቲ ሜትር በደረሰ በረዶ መሸፈናቸውን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡
የኒውዮርክ አስተዳዳሪ ካቲ ሆቹል፣ ከአውሎ ነፋሱ በፊት በአስተዳደሩ ከግማሽ በላይ ለሚሆኑ ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡
ክስተቱንም ተከትሎ ከትናንት ጀምሮ በአብዛኛው በኒውዮርክ አካባቢ ከ900 በላይ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን፣ ከ8 ሺህ በላይ በረራዎች ደግሞ በመላ ሀገሪቱ እንዲዘገዩ መደረጉን የበረራ ቁጥጥር ድረ-ገፅ ያወጣው መረጃ ማመለካቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በታምራት ቢሻው