AMN – ታኅሣሥ 20/2018 ዓ.ም
የግሉ የንግድ ዘርፍ ስነ-ምግባርን በተላበሰ አሰራር ማህበረሰቡን ሊያገለግል ይገባል ሲሉ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሐመድ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከግሉ ዘርፍ እና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር የፓናል ዉይይት እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሐመድ፤ የግሉ ንግድ ዘርፍ ስነ-ምግባርን በተላበሰ አሰራር ማህበረሰቡን ሊያገለግል ይገባል ብለዋል።

በተለይም የግሉ ዘርፍ ስራውን ሲሰራ የሞራል ተጠያቂነትን እያሰበ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
መሰል የዉይይት መድረኮች ችግሮች ስር ሳይሰዱ መፍትሔ እንዲያገኙ ያስችላሉ ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ በንግዱ ዘርፍ አዎንታዊ ውጤት እየተመዘገበ ቢሆንም በመልካም አስተዳደር በኩል ክፍተቶች እንዳሉ አንስተዋል።
በመድረኩ ለሀገራዊ እድገት የግሉ ዘርፍ የድርሻውን እንዲወጣ መንግስት ምቹ መደላድሎችን ሊፈጥር ይገባል ተብሏል።

የውይይት መድረኩ በኢንቨስትመንት፣በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙርያ እና የተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን በተመለከተ ትኩረቱን አድርጓል።
በትባረክ ኢሳይያስ