የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል

You are currently viewing የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል
  • Post category:አፍሪካ

AMN ታህሳስ 21/2018

ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም የካቲት 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሴኤ) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁነቱን ያዘጋጃል።

ፎረሙ በአዲስ አበባ በየካቲት ወር ከሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሚደረግ ነው።

“የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ በፋይናንስ መደገፍ፤ ስራ እና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ትራንስፎርሜሽን” የፎረሙ መሪ ሀሳብ ነው።

የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ አህጉራዊ የምክክር መድረክ መሆኑን ከኢሲኤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አህጉራዊው መድረክ የአፍሪካ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያንና የልማት አጋሮችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው።

ፎረሙ አጋርነትና የኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ በተለይም የመንግስት እና የግል የተቀናጀ የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ይደረጋል።

የስራ ዕድል፣ ምቹ የኢኖቬሽን ስነ ምህዳር እና የአፍሪካን የፈጠራ አቅም አሟጦ መጠቀም በፎረሙ ላይ ምክክር ከሚካሄድባቸው አጀንዳዎች ይጠቀሳሉ።

በተለይም የዲጂታል ኢንዱስትሪዎች፣ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም እየሰፋ ያለውን የአፍሪካ የፈጠራ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review