የኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ እንደ ዋና የቡና እና የባህል መዳረሻ ለማስቀመጥ ትኩረት ያደረገ የመገናኛ ብዙሃን ጉብኝት በደቡብ ኢትዮጵያ ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ አካሂደዋል።
የቡና ቱሪዝምን ለማሳደግና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለመጨመር በዘርፉ ላይ የተሰማሩትን አርሶ አደሮች ማበረታታት ተገቢ ስራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ባህላና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናን በሰፊው በማምረት ጌዴኦ ዞን ትልቁን ቦታ ይይዛል ያሉት ኃላፊዋ፣ ቡና ማህበራዊ መስተጋብርን በማጠናከር በማህበረሰቡ የየዕለት እንቅስቃሴ ውሰጥ ትልቅ ቦታን ይይዛል ብለዋል።
ከለውጡ ዓመታት በኋላ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ በተደረገው የሪፎርም ስራ ትልቅ ለውጥና መነቃቃት መጥቷል፣ ኢትዮጵያውያን በቡና ምርት ላይ ያለንን የረጅም ጊዜ ባህልና ታሪክን በመጠቀም፣ በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ዕረገድ ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቀናል ብለዋል።
በኢትዮጵያውያን የየዕለት እንቅሰቃሴ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን የቡና ታሪክና ባህላዊ እሴትን ለዓለም ማስተዋወቅ ተገቢ መሆኑን በቱሪዝም ሚኒሰቴር የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው ተናግረዋል።
በካስዬ ማንጉዳ