ፔዳልፍላይ የተባለ ስታርትአፕ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በመጠቀም በአዲስ አበባ ውብ ኮሪደሮች ላይ ደንበኞቹን አምኖ ብስክሌት በማከራየት ምሳሌ መሆኑን ብሔራዊ መታወቂያ አስታዉቋል።
ስታርታፕም ሆኑ ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይህን ተሞክሮ በመውሰድ አገልግሎታቸዉን ወይም ሲስተማቸዉን ከፋይዳ ጋር በማጣመር በኤሌክትሮኒክ ደንበኛህን እወቅ (eKYC) ለደንበኞች አስተማማኝ አገልግሎትን መስጠት እንደሚችሉ ገልጿል።
ፋይዳ የዲጂታል ኢትዮጵያ ዋነኛ ምሰሶ የሆነውን “መተማመንን” የሚያሰፍን ስርዓት እየዘረጋ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ከብሔራዊ መታወቂያ ያገኘነዉ መረጃ መሠረት በአገልግሎት ሰጪዎችና በደንበኞች መካከል መተማመንን የሚፈጥረዉ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በአሠሪና ሠራተኛ፣ በአከራይና ተከራይ እንዲሁም በሌሎች ውል ሰጪና ተቀባዮች መካከል “መተማመንን” በማስፈን ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በወንድማገኝ አሠፋ