አርሰናል አስቶንቪላን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

You are currently viewing አርሰናል አስቶንቪላን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

AMN ታኅሣሥ 21 ቀን 2018 ዓ.ም

በ19ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር በሜዳው ኤምሬትስ አስቶንቪላን ያስተናገደው አርሰናል በድንቅ ብቃት 4ለ1 አሸንፏል። ጋብርኤል ማጋሌሄሽ ፣ ማርቲን ዙብሜንዲ ፣ ሊአንድሮ ትሮሳርድ እና ጋብርኤል ጄሱስ የመድፈኞቹን ግብ አስቆጥረዋል።

የአስቶንቪላን ልዩነት ያልፈጠረች ግብ ኦሊ ዋትኪንስ አስመዝግቧል። በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ሙሉ ብልጫ የወሰደው አርሰናል ለምን በበርካቶች ዘንድ ዋንጫ የማሸነፍ ግምት እንደተሰጠው አሳይቷል።

ካደረጋቸው 19 ጨዋታ 45 ነጥብ የሰበሰበው አርሰናል ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት አስፍቷል። ሲቲ ከነገ በስቲያ ከሜዳው ውጪ ከሰንደርላንድ ጋር ይጫወታል።

በተመሳሳይ ሰዓት የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር አቻ ተለያይቷል። ጆሹአ ዚርክዜ ለዩናይትድ ላንዲስላቭ ክሩይች ለዎልቭስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዎልቭስ የውድድር ዓመቱን ሦስተኛ ነጥብ አግኝቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review