የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተማሪዎች በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ እና ህልማቸውን እንዲያሳኩ በታላቅ ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተማሪዎች በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ እና ህልማቸውን እንዲያሳኩ በታላቅ ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል

AMN – ታኀሣሥ 22/2018 ዓ/ም

የከተማ አስተዳደሩ ነገን የመስራት ራዕይን አንግቦ በሰራው ሥራ በአዲስ አበባ በት/ቤት ምገባ 940 ሺህ 329 ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ተማሪዎች በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይሰናከሉና ህልማቸውን እንዲያሳኩ በታላቅ ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

በመሆኑም ዛሬ ላይ 940 ሺህ 329 ተማሪዎች የዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ከፍ በማድረግ፣ ትምህርት የማቋረጥ ምጣኔን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ የፕሮግራሙ ዋና ዋና ስኬቶች ናቸው፡፡

በተጨማሪም የህፃናትን አካላዊ ጥንካሬ፣ አእምሯዊ ንቃትና ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነት በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ቁርስ፣ ምሳ እና የትምህርት ቁሳቁስ (ደብተር፣ ዩኒፎርም፣ የንፅህና መጠበቂያ) የነበረባቸውን የኢኮኖሚ ጫና በማቃለል ሰላምና እረፍት ሰጥቷል።

አስተዳደሩ የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲን በማቋቋም ድጋፉ ወጥ፣ ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ መሆኑን እያረጋገጠ ይገኛል። ይህ ተግባር የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማስፈን የተወሰደ ትልቅ እርምጃ መሆኑ የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review