የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2026 የፈረንጆች አዲስ ዓመት መለወጫን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ለሚገኙ አምባሳደሮች፣ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ለኢትዮጵያ ወዳጆች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባዋ በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ባስተላለፉት በዚህ መልዕክት፤ አዲሱ ዓመት የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም ባለፈው የሥራ ዘመን በከተማ አስተዳደሩ እና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መካከል የነበረውን ጠንካራ ግንኙነት አድንቀዋል።
በመጪው 2026 ዓመትም ይህ የሁለትዮሽ ወዳጅነት እና የልማት ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።