በዓለም ዙሪያ ያለዉ የፈረንጆቹ አዲስ አመት በዓል አከባበር ምን ይመስል ይሆን?

You are currently viewing በዓለም ዙሪያ ያለዉ የፈረንጆቹ አዲስ አመት በዓል አከባበር ምን ይመስል ይሆን?

AMN -ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም

የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በተለያዩ የዓለም ሀገራት በልዩ ልዩ ሥነ ሥርዓቶች ይከበራል፡፡ በርካታ የዓለም ሃገራትም 2026 አዲስ ዓመትን በተለያዩ መርሃ ግብሮች በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡

ለመሆኑ በዓለም ዙሪያ ያለዉ የአዲስ አመት አከባበር ባህል ምን ይመስል ይሆን?

ስፔኖች አዲሱን አመት ለመቀበል እኩለ ለሊት ላይ 12 የወይን ፍሬዎችን ይመገባሉ፡፡ ለአስራ ሁለቱ ወራት ዕድል ይሆን ዘንድ፣ ለእያንዳንዱ የሰዓት ደወል አንድ ወይን ፍሬ በመመገብ እለቱን ያከብራሉ፡፡

ዴንማርኮች እለቱን የሚቀበሉት ከወንበር ላይ በመዝለል ሲሆን ክፉ መናፍስትን በማባረር ወደ አዲሱ ዓመት በቀጥታ ለመዝለል ነዉ የሚል ትርጉም ይሰጡታል፡፡

ኮሎምቢያኖቹ ደግሞ ባዶ ሻንጣ ይዘዉ በመጓዝ ነዉ አዲሱን አመት የሚቀበሉት፡፡ ይህም አዲሱ አመት የጉዞ እና የጀብዱ ዓመት እንዲሆን ያደርጋል ተብሎ ይታመናል፡፡

ብራዚሎች ነጭ፤ ፊሊፒንሶች ደግሞ ነጠብጣብ ያለዉ ልብስ በመልበስ አዲሱን አመት ይቀበላሉ፡፡

ግሪኮች የሮማን ፍሬ በመፈጭትና በመሰባበር የሚያከብሩ ሲሆን ይህም ዘር በበዛ ቁጥር፣ ለቤት ጤና እና ብልጽግና ይበዛል የሚል አመኔታ አለዉ፡፡

ጃፓኖች ኑድልስ የሚመገቡ ሲሆን ይህም ረጅም ዕድሜን ይወክላል የሚል እምነት አላቸዉ፡፡ በቀላሉ የሚቆረጡ በመሆናቸውም ካለፈው ዓመት መከራዎች ጋር “ንጹህ መለያየትን” ያመለክታሉ።

ጣሊያኖች ምስር በመብላት አዲሱን አመት የሚያከብሩ ሲሆን ጠፍጣፋና ሳንቲም መሰል ቅርጻቸው የገንዘብ ስኬትን ወይም ሀብትን ያመጣል ብለዉ ያምናሉ፡፡

ለመሆኑ እርስዎ በሚገኙበት የዓለም ክፍል የፈረንጆቹ አዲስ አመት በምን አይነት ሥነ ሥርዓቶች ይከበር ይሆን? ያጋሩን !

በወንድማገኝ አሰፋ

#Ethiopia

#AddisAbaba

#NewYear2026

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review