46 ዋንጫ ያነሳው አሰልጣኝ

You are currently viewing 46 ዋንጫ ያነሳው አሰልጣኝ

AMN ታኅሣሥ 22/ 2018 ዓ.ም

የተወለዱት በስኮትላንድ መዲና ግላስኮ ነው ፡፡ ከዛሬ 84 ዓመታት በፊት በሐገራቸው ዝነኛ ክለብ ሬንጀርስን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች በአጥቂ ስፍራ ተጫውተው አሳልፈዋል፡፡

አሌክዛንደር ቻፕማን ፈርጉሰን የማንችስተር ዩናይትድ የቀድሞ ስኬታማ አሰልጣኝ ከተወለዱ ዛሬ 84 ዓመት ሞላቸው፡፡

ተጨዋችነታቸው ባበቃ ማግስት ወደ አሰልጣኝነቱ የገቡት ፈርገሱን በማንችስተር ዩናይትድ የ27 ዓመታት ቆይታቸው ለቁጥር የሚያዳግቱ ስኬቶችን ማስመዝገባቸው ይታወሳል፡፡

የብሪታንያ መንግስት በየጎራው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሰዎች የሚሰጠውን የ‹‹ሰር›› ማዕረግ ያገኙት አሌክስ ፈርጉሰን በኦልድትራፎርድ ቆይታቸው በስማቸው የሚጠሩ ተጨዋቾችን ጭምር ማፍራት የቻሉ ስኬታማ አሰልጣኝ ናቸው፡፡

በዩናይትድ ቆይታቸው ብቻ 13 የፕሪምየር ሊግ፣ 10 የእንግሊዝ ሱፐር ካፕ፣ አምስት የኤፍ ኤ፣ አራት የሊግ ካፕ፣ ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ ኢንተር ኮንቲኔንታልና አንድ የዓለም ክለቦች ዋንጫን አንስተዋል፡፡

በስኮትላንድ የአሰልጣኝነት ዘመናቸውም ሶስት የስኮቲሽ ሊግን፣ አራት የስኮቲሽ ዋንጫን፣ እንዲሁም አንድ የስኮቲሽ ሊግ ካፕን በድምሩ 46 ዋንጫዎችን ያነሱት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ዛሬ 84ኛ ዓመት ልደት በዓላቸውን እያከበሩ ነው፡፡

በ2013 ከአሰልጣኝነት ስራቸው በገዛ ፍቃዳቸው ጡረታ የወጡት ሰር አሌክስ የዕረፍት ጊዜያቸውን ማንችስተር ዩናይትድን በማማከር፣ የክለቡን ጨዋታዎች በመመልከት እያሳለፉ ነው፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review