አዲስ አበባን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ በማድረግ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ ነው

You are currently viewing አዲስ አበባን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ በማድረግ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ ነው

AMN | ታኅሣሥ 23/2018 ዓ.ም.

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ ማድረግ ያስቻሉ ተግባራትን በቅንጅት በማጠናከር የከተማዋን የቱሪስት ተደራሽነት እናሳድጋለን ሲል የከተማዋ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው የከተማዋን ጽዳትና ውበት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። በሥልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)፥ አዲስ አበባ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባከናወነቻቸው የጽዳትና ውበት ተግባራት የዓለምን ትኩረት መሳብ መቻሏን ገልጸዋል።

ይህ የከተማዋን የቀድሞ ገጽታ የቀየረና በዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር እውቅናን ያስገኘ የጽዳትና ውበት ሥራ ይበልጥ በማጠናከር የከተማዋን የቱሪስት ፍሰት ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል ዋና ሥራ አስኪያጁ። ከተማዋን በጽዳትና ውበት ሞዴል እንዳደረግናት ሁሉ፣ አጠቃላይ የቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ሥርዓቱን በማዘመን ከዘርፉ በመልሶ መጠቀም የሚገኘውን ሀብት ማሳደግ ይገባልም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ በበኩላቸው፣ በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የአመራሩንና የባለሙያውን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸው፣ ይህም ተቋሙ እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ፈጣን፣ ዘመናዊና ውጤታማ ለማድረግ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

“ተደምረን አዲስ አበባን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ በማድረግ የቱሪስት መዳረሻ እናደርጋታለን” በሚል መሪ ቃል መሰጠት በጀመረው ሥልጠና ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ የዘርፉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review