ከሙዚቃ ጋር ተዋህደዉ በከፍተኛ፣ በመካከለኛ እና በዝቅተኛ ከፍታ ላይ እንዲፈነዱ የሚደረጉ ሰማዩን ወደ ግዙፍ ሲኒማነት የቀየሩ የዘመኑ ርችቶች

You are currently viewing ከሙዚቃ ጋር ተዋህደዉ በከፍተኛ፣ በመካከለኛ እና በዝቅተኛ ከፍታ ላይ እንዲፈነዱ የሚደረጉ ሰማዩን ወደ ግዙፍ ሲኒማነት የቀየሩ የዘመኑ ርችቶች

AMN ታኅሣሥ 23 /2018 ዓ.ም

የፈረንጆቹን እና የኢትዮጵያዊያንን አዲስ አመት ጨምሮ በሰርግ፤ በልደትና በተለያዩ በዓላት ላይ ማድመቂያ ርችትን መጠቀም የተለመደ ተግባር ነዉ፡፡

ለመሆኑ ርችት መጠቀም እንዴት ተጀመረ?

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ለበዓላት ማድመቂያ የምንጠቀምባቸው ርችቶች ረጅም እና አስደናቂ ታሪክ አላቸዉ፡፡ የርችት ዝግመተ ለውጥ ከጥንታዊቷ ቻይና የቀርከሃ ፍንዳታ ተነስቶ ዛሬ በኮምፒውተር ረቂቅ ጥበብ ላይ ደርሷል፡፡

ከመድሃኒት ፍላጋና ከባሩድ ግኝት ጋር ተያያዥነት ያለዉ የርችት ታሪካዊ አመጣጥ በጣሊያን ኬሚስቶች ዘመናዊ መልክ እየያዘ መምጣቱን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

ርችቶቹ በተለይ እንደ ቀይ፣ ሰማያዊ እና አረንጓዴ ያሉ ደማቅ ቀለማትን ለመጀመሪያ ጊዜ እየፈጠሩ የመጡት በዚሁ ጊዜ ነበር፡፡

ከዘመናት በኋላ ግን ርችቶቹ ከሰዉ እጅ በመዉጣት በኮምፒዉተር ቴክኖሎጂ ጭምር መታዘዝ ጀምረዋል፡፡

የዘመናችን ርችቶች የኬሚስትሪ እና የፊዚክስ ውጤቶች በመሆናቸዉ በኮምፒውተር ትዕዛዝ እና በኤሌክትሮኒክስ አማካኝነት በታቀደላቸው ሰከንድ ላይ በትክክል መፈንዳት ችለዋል፡፡

የአለማችን የርችት ዲዛይነሮች በሰማይ ላይ የሚታዩትን ቅርጾች እና ቀለማትን ለመፍጠር የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡

በርካታ ሃገራትም ርችቶችን ከሙዚቃ ጋር አዋህደዉ በከፍተኛ፣ በመካከለኛ እና በዝቅተኛ ከፍታ ላይ እንዲፈነዱ በማድረግ ሰማዩን ወደ ግዙፍ ሲኒማነት በመቀየር ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁን ላይ ከድምጽ ጋር ተዋህደዉ የሚለቀቁ ርችቶችን መመልከት የደስታ ስሜትን ብቻ ሳይሆን ግርምትን ጭመር የሚፈጥሩና የሰዉ ልጆችን የፈጠራና የምርምር አቅም የሚገልጡ ሆነዋል፡፡

ከቀርከሃ እስከ ጠፈር፤ የፋየርዎርክስ(ርችት) የደረሰው የርችት ጥበብ እና ታሪክ በድሮንና በሌሎች መሰል ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የአለማችን የበዓላት ማድመቂያ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review