በ19ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብሩ ሊድስ ዩናይትድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ጨዋታውን ያለግብ አጠናቋል።
በአንፊልድ የተደረገው ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ግልፅ ግብ የማግባት ዕድል አልተፈጠረበት።
ሊድስ ተቀይሮ በገባው ዶሚኒክ ካልቨርት ሊውን ግብ ቢያስቆጥርም ከጫወታው ውጪ በመሆኑ ተሽሯል።
ሊቨርፑል በሊጉ ከሦስት ተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ጥሏል።
ከ19 ጨዋታ 33 ነጥብ የሰበሰበው ሊቨርፑል 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የፊታችን እሁድ ማንችስተር ዩናይትድን በኤላንድ ሮድ የሚያስተናግደው ሊድስ በ21 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ እና ፉልሀም 1ለ1 ተለያይተዋል።
ዦን ፍሊፕ ማቴታ ለፓላስ ፣ ቶም ኬርኒ ለፉልሃም ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ